Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በአርባ ምንጭ ከአንድ ግለሰብ ሆድ ውስጥ በርካታ የተለያዩ የስለት መሳሪያዎች በቀዶ ጥገና ሕክምና ወጣ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 20፣ 2013 ― በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአንድ ታካሚ ሆድ ውስጥ በርካታ የተለያዩ የስለት መሳሪያዎች በቀዶ ጥገና ሕክምና ሊወጣ እንደቻለ ሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ ገልጸዋል፡፡

በሆስፒታሉ የታካሚውን የሕክምና መረጃ መሠረት አድርጎ በተደረገው የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች ባደረጉት ክትትል እና በጨረር ምርመራ የተለያዩ ስለት ያላቸው ቁሳቁሶችና እስክሪብቶ ጨምሮ ከሆዱ ሊገኝ ችሏል ነው የተባለው፡፡

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ እንዳስታወቁት ታካሚው ታራሚ እና የአዕምሮ በሽተኛ መሆኑን በመግለጽ፣ የቀዶ ህክምናው የተደረገው ከዕለታት ባንዱ ቀን እስክሪብቶ ሲውጥ ያየ ሌላ ግለሰብ ባደረገው ጥቆማ መሠረት ነው ብለዋል።

በታካሚው ሆድ ውስጥ የነበሩ በርካታ ምስማሮች፤ እስክሪቢቶና ሌሎች የስለት ቁሳቁሶች በቀዶ ሕክምና መውጣቸውንም አስረድተዋል። ስለት እና ሌሎች ቁሳቁሶች የተገኙበት ታካሚ ከቀዶ ሕኪምና በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የዘገበው የደቡብ ራድዮ እና ቴሌቪዥን ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img