Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በጀርመን ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ ከሁለት ዓመት ልጇ ጋር ተገደለች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 20፣ 2013 ― በጀርመን ባየርን ክሮናህ ከተማ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት ከእነ ሁለት ዓመት ልጇ መገደሏ ተሰምቷል፡፡ ቢቢሲ የሟች ሃይማኖት ገ/እግዚአብሔር የቅርብ ጓደኞች ነግረውኛል ብሎ እንደዘገበው ኢትዮጵያዊትዋ ባለፍነው እሑድ ግንቦት 15፣ 2013 አመሻሽ ላይ የተገደለችው የሞሮኳ ዜግነት ባለው የቀድሞ የፍቅር አጋሯ ነው፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ በራሱም ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ኋላም በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

ላለፉት ሰባት ዓመታት ገደማ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ እንደኖረች የተነገረው በ30ዎቹ መጀመሪያ እድሜ ላይ የነበረችው ሟች ሃይማኖት ገብረ እግዚአብሔር፣ ከሁለት ዓመት ልጇ ጋር ነው ግድያው የተፈጸመባት፡፡

ፍራንክንፖስት የተባለ ያገሩ ጋዜጣ የኮበርግ ወንጀል ምርመራ ቡድንና ዐቃቤ ሕግን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ግለሰቡ እናትና ልጅ ወደሚኖሩበት ቤት ሕንጻ በማምራት በቢላ ወግቶ ሳይገላቸው እንዳልቀረ ከፍተኛ ጥርጣሬ አለ፡፡

ግድያው በተፈጸመበት ወቅት በወቅቱ በሕንጻው ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሦስት ሴቶች ተሯሩጠው በመውጣት ለፖሊስ እንደደወሉ ጋዜጣው የጠቀሰ ሲሆን፣ በእናትና ልጅ መኖሪያ ቤት ውስጥ እሳት የተነሳውም በዚህ ጊዜ እንደነበር ነው ያመለከተው፡፡

ግለሰቡ ሆነ ብሎ እናትና ልጅ ላይ እሳት እንደለኮሰ ፖሊስ ጥርጣሬ እንዳለው ‘ፍራንክንፖስት’ ዘግቧል።

የእናትና ልጅ አስክሬንም የተገኘው በእሳት አደጋ ሠራተኞች ነበር። እንደ ጋዜጣው ከሆነ ግለሰቡም በእሳቱና ከበረንዳ ላይ ዘሎ ለማምለጥ በመሞከሩ ለሕይወቱ አስጊ የሆነ ጉዳት ደርሶበታል።

የእናትና ልጅ የአስክሬን ምርመራ ውጤት የሁለት ዓመቷ ህጻን በቢላ በመወጋቷ ሕይወቷ ሲያልፍ፤ እናቷ ግን በስለቱ ጉዳት ቢደርስባትም እሳቱ ከተነሳ በኋላ ሕይወቷ ማለፉን ያሳያል ተብሏል።

ቢቢሲ አንደኛው የሟች ጓደኛ ነገረችኝ እንዳለው፣ ኢትዮጵያዊቷን የገደለው ግለሰብ ከሟች ጋር ለወራቶች የዘለቀ የፍቅር ግንኙነት ነበራቸው። በካምፑ ውስጥ ሁለቱም ለየብቻ ነበር የሚኖሩ ሲሆን፣ ነገር ግን ጎረቤት ነበሩ። ሆኖም በባህልም፣ በባህርይም ልዩነት ባለመግባባታቸው ግንኙነታቸው ባለመዝለቁ ቢለያዩም እርሱ ግን ከእርሷ ጋር መለያየት አልፈለገም ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img