Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በሾፌሮች ትከሻ ላይ ወድቋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 19፣ 2013 ― የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል የሲሚንቶና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶችን በወቅቱ ለማድረስ ብርቱ የትራንስፖርት ችግር መከሰቱ ተነግሯል፡፡

እንደ ዋዜማ ራድዮ ዘገባ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ስድስት የከባድ ደረቅ ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከጣሊያኑ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ሳሊኒ ጋር ውል በማሰር ይሰጡ የነበረ ሲሆን፣ በአገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ እና እና በሌሎችም ምክንያች የሲሚንቶና ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች አቅርቦት የተፈለገውን ያህል አልነበረም።

ይህን ተከትሎ የፌደራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን የትራንስፖርት ማኅበራት እና ድርጅቶች ኮታ ተሰጥቷቸው ከሳሊኒ ጋር ውል በማሰር እንዲያስሩ ምከረ ሐሳብ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም የሚፈለገውን ለውጥ አላመጣም።

ከዚህ ተደጋጋሚ ጥረት በኋላ የትራንስፖርት ባለስልጣን ቀጣዩ የመፍትሔ ሃሳብ የነበረው ለትራንስፖርት ድርጅቶችና ማኅበራት ጥሪ ማድረግ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በሚፈልገው መጠን ምላሽ ማግኘት አለመቻሉን ነው የተነገረው፡፡

በኋላም መንግስት የትራንስፖርት ማኅበራት እና ድርጅቶችን ከመብራት ኃይል ጋር ውል አስረው በአስገዳጅ ሁኔታ የሚሰሩበት አሰራርን አውጥቷል፡፡ ይህ የፌደራል ትራንሰፖርት ባለስልጣን ያወጣው አስገዳጅ አሰራር የትራንስፖርት ድርጅቶችና ሾፌሮች በሳምንት የተሰጣቸውን ኮታ ሳያጠናቅቁ ወደ ጅቡቲ እንዳይንቀሳቀሱ የሚያግድ ነው፡፡

ነገር ግን ባለስልጣኑ ያወጣውን መመሪያ ጉድለቶች የነበሩትና ለሙስና በር የከፈተ ስለነበር ሁነኛ መፍትሔ መሆን አልቻለም ነው የተባለው። አሽከርካሪዎቹ ስራውን ላለመስራት ከሚያቀርቧቸው ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ እና በተለያዩ ጊዜያት እየተደጋገመ የመጣው የሾፌሮች ግድያ ይጠቀሳል፡፡

እንደመጨረሻ አማራጭ የትራንስፖርት አስሪዎች ፌድሬሽን በከባድ ደረቅ ጭነት ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ባለንብረቶችን ኃላፊነታቸውን እና ግዴታቸውን እንዲወጡ በዚህ ሳምንት በይፋ ጥሪ ሊቀርብላቸው እንደሆነም ተሰምቷል፡፡

የሕዳሴ ግድብን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በሐምሌ ወር ለማካሄድ ዕቅድ እንደተያዘ የሚታወቅ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img