Friday, November 22, 2024
spot_img

ሁሉም አካላት በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመክሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠየቁ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሁሉም አካላት በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመክሩ ዛሬ በተጀመረው ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ መክፈቻ ላይ ጠይቀዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የጉባኤውን መከፈት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የሁሉም ነገር መሰረትና የችግሮች ሁሉ መፍትሔ ሰላምና ሰላም ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚሁ ንግግራቸው ወቅት ‹‹ለመንግስት ሆነ ለሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ማስተላለፍ የሚፈልገው የአደራ መልዕክት ቢኖር፣ የሁሉም ነገር መሰረት እና የችግሮቻችን ሁሉ መፍትሔ ሰላም እና ሰላም ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ለሰላም ሲባል አስፈላጊ የሆነ ዋጋ መክፈል እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ነው›› ሉት ብጹእ አቡነ ማትያስ፣ ‹‹ዋስትና ያለው ሰላም በሀገራችን ሊረጋገጥ የሚችለው ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰባስበው መወያየት፣ መግባባትና ሀገራዊ ስምምነት መፈፀም ሲችሉ›› መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስለሆነም ይህ ለነገ የማይባል፣ የህልውናችን ጥያቄ መልስ መሆኑን አውቀን ሁላችንም በዚህ መልካም ስራ እንተባበር ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img