Sunday, October 6, 2024
spot_img

አቶ ሽመልስ ዐብዲሳ ከአሜሪካ ማዕቀብ ነቀዝ የበላው ስንዴ ነው የሚቀርብን ሲሉ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ ዐብዲሳ ከሰሞኑ አሜሪካ ከጣለችው ማዕቀብ የሚቀርብን ‹‹ነቀዝ የበላው ስንዴ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን የተናገሩት በትላንትናው እለት በሸራተን ዐዲስ የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ፋሲል ከነማ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ባካሄደበት ወቅት ባሰሙት ንግግር ነው፡፡

በዚህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎችም በተገኙበት መድረክ ከሰሞኑ በአሜሪካ በኩል ቪዛ መከልከሉን ያነሱት አቶ ሽመልስ፣ ‹‹እኔን አያውቁኝም እኔም አላውቃቸውም፣ ብዙም አይመለከተኝም›› ተደምጠዋል፡፡

አቶ ሽመልስ ዐብዲሳ አክለውም ‹‹ሞያሌና አድዋ ለመሄድ ቪዛ አያስፈልገኝም›› ያሉ ሲሆን፣ ‹‹እንኳን ሁሉም ፊቱን አዞረብን፣ ተባብረን ወገባችንንን ጠበቅ አድርገን እንረስ፣ አገራችንን ከዚህ ውርደት እንታደጋት፣ ባለፈው መቶ ዓመት በነሱ አዙሪት ውስጥ አገሪቱ ከርማለች›› የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በተጨማሪም ‹‹የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ሞላ ብለው ይደራደሩ፣ እንቢ ካሉም ጥለው ይምጡ፣ አርሰን ኤክስፖርቱን እየጨመርን አገራችንን ከውርደት እንታደግ›› ብለዋል፡፡

ይኸው የአቶ ሽመልስ ዐብዲሳ ንግግር ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን ጨምሮ ከመድረኩ በጭብጨባ ምላሽ ተሰጥቶታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img