Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ሕወሓት እስካሁን ድረስ 22 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን መግደሉን መንግሥት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― ከፌዴራል መንግሥት ጋር እየተዋጋ የሚገኘው ሕወሃት እስካሁን ድረስ 22 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን መግደሉን በመንግሥት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ 20 የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት በሕወሓት መታገታቸውን እና 4 የአስተዳደሩ አባላት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ሆስፒታል መግባታቸውን የመረጃ ማጣሪያው ጨምሮ ገልጿል፡፡

ማጣሪያው አክሎም እየታገልኩ ያለሁት ለትግራይ ሕዝብ ነው የሚለው ሕወሓት ይልቁንም የክልሉን ሐብት እያወደመ እንዲሁም በክልሉ መረጋጋትን ለማምጣት የሚሰሩ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላትን እየገደለና እያገተ መሆኑን የጠቆመ ሲሆን፣ አሁንም መኖሪያ ቤቶችን እንደሚያቃጥልም ነው የገለጸው፡፡

ሕወሃት ጥቃቱን ፈጽሞባቸዋል የተባለው በትግራይ ደቡብ ዞን፣ በተምቤን፣ በምብራቅ፣ ደቡባዊ ምብራቅ፣ በማእከላዊ ዞን፣ በሰሜን ምሥራቅ እና በመቀሌ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img