አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― የአውሮፓ ኅብረት ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኮሚሽነር ዩታ ኡርፒላይነን እና የኅብረቱ የቀውስ አስተዳዳር ኮሚሽነር ያኔዝ ሌላርቺች ከአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ጅፍሪ ፌልትማን ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡
የአውሮፓ ኅብረት ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኮሚሽነር ዩታ ኡርፒላይነን በትዊተር ገጻቸው ላይ ገንቢ ነበር ባሉት ምክክር ላይ በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ችግር ለመግታት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተቀናጀ አቀራረብ ሊኖረው እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስፍረዋል፡፡