Saturday, September 21, 2024
spot_img

የሶማሊ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ወደ ወለድ አልባ ባንክ ሊያድግ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― የሶማሊ ብድር እና ቁጠባ ተቋም በምሥረታ ላይ ከሚገኝ ሌላ ባንክ ጋር ጥምረት በመፍጠር ‹‹ሸበሌ›› በሚል ሥያሜ ወደ ወለድ አልባ ባንክ ሊያድግ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በ2003 የተመሠረተው የሶማሊ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ጥምረት የሚፈጥረው በሶማሊ ማኅበረሰብ እየተቋቋመ ከነበረ ‹‹ሸበሌ›› ከተባለ ወለድ አልባ ባንክ ጋር መሆኑን የዘገበው ካፒታል ጋዜጣ ነው፡፡

የሶማሊ ብድር እና ቁጠባ ተቋም እና በምሥረታ ላይ የነበረው ወለድ አልባ ባንክ ሰዎች በቅርቡ በክልል መቀመጫ ጂግጂጋ ተገናኝተው በመምከር ነው ሸበሌ የተሰኘውን የባንኩን ሥያሜ በጋራ ለመጠቀም የወሰኑት፡፡

የሶማሊ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ኸድር አሕመድ እንደገለጹት፣ ይህንኑ ወደ ባንክ የማሳደግ ውጥን ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ እየተዘጋጁ ይገኛሉ፡፡

የሶማሊ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ባንክ ለመመስረት ያስፈልጋል የሚባለውን ግማሽ ቢሊዮን ብር ካፒታል እንዳሟላ የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ኸድር አሕመድ፣ አሁንም ቢሆን የሶማሊ ማይክሮ ፋይናንስ ተጨማሪ አክሲዮን በመሸጥ ካፒታሉን ያሳድጋል ብለዋል፡፡ ወደ ወለድ አልባ ባንክ ለማደግ እየተንደረደረ የሚገኘው የሶማሊ ብድር እና ቁጠባ ተቋም፣ በተለይ በሞባይል ባንኪንግ አሠራሩ ስኬታማ እንደሆነ የሚነገርለት ነው፡፡

በተመሳሳይ በቅርቡ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ‹‹ፀደይ›› በሚል እና የኦሮሚያ ማይክሮ ፋይናናስ ደግሞ ከሰሞኑ ‹‹ሲንቄ›› በሚል ሥያሜ ወደ ባንክነት ሽግግር ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img