Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ኤርትራ ሁሉንም ወታደሮቿን እንድታስወጣ መጠየቃቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 18፣ 2013 ― የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን የፌዴራል መንግስት እና የሕወሃትን ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ መሬት የዘለቁ ሁሉም የኤርትራ ወታደሮች እንዲወጡ መጠየቃቸውን ብሉምበርግ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ጉዳዩን አስመልክቶ ለኤርትራው አቻቸው ደብዳቤ ከጻፉ በርካታ ቀናት ማስቆጠሩ ነው የተነገረው፡፡

ብሉምበርግ ጉዳዩን ለማረጋገጥ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቃል አቀባይ ቢልለኔ ሥዩም እና ለኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል የጽሑፍ መልእክት ባስቀምጥም ምላሽ አልሰጡበትም ብሏል፡፡

በጥቅምት ወር የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ መሬት የዘለቁት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል የተለያዩ ግድያዎችን እና አሰቃቂ ተግባራትን መፈጸማቸው ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወታደሮቹ የኢትዮጵያን መሬት ለቀው ይወጣሉ ካሉ ስምንት ሳምንታት ያለፈው ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ አለመውጣታቸው ነው የሚነገረው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img