አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 17፣ 2013 ― በትግራይ ክልል ከዛሬ ግንቦት 17 ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት “ፆመ ትግራይ” በተደረገው ጥሪ መሠረት አገልግሎቶች በሙሉ መዘጋታቸው ታውቋል።
በትላንትናው ዕለት የንግድ ድርጅቶች እንዲዘጉ፣ የታክሲ እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ፣ መንግስት ሰራተኞች ስራ እንዳይገቡ፣ ሁሉም ሰው ስልክ እንዲዘጋ የሚሉ መልዕክቶችን የያዙ ወረቀቶች በመቀሌ ከተማ መበተናቸው ተነግሯል።