Monday, October 7, 2024
spot_img

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በእነ አቶ ስብሐት ነጋ ላይ ተገድጄ አልመሰክርም ማለታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 17፣ 2013 ― የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ እብራሂም ለፍርድ ቤት ቃላቸውን መስጠታቸው ተሰምቷል።

በዛሬው ችሎት በእነ አቶ ስብአት ነጋ ላይ ለመመስከር ራሳቸውን አስመዝግበው የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ እብራሂም በዛሬው ቀጠሮ አልመሰክርም ማለታቸው ነው የተሰማው።

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ በነበረው ቀጠሮ በእነ አቶ ስብሓት ነጋን ጨምሮ 42 ተጠርጣሪዎች ላይ የዓቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመስማት የተቀጠረ ሲሆን፣ በቀዳሚነት በምስክርነት የቀረቡት ወ/ሮ ኬሪያ ልታሰር እንጂ በነሱ ላይ አልመሰክርም ማለታቸው ተነግሯል።

ወ/ሮ ኬሪያ በችሎቱ እንዲመሰክሩ ቢቀርቡም ለፍርድ ቤቱ መመስከር ካለብኝ እንኳ የምመሰክረዉ ይህ መንግሥት በትግራይና በኢትዮጵያ እናቶች፣ ሕፃናትና ሕዝብ ላይ የሚያደርገውን ጭፍጨፋ ከሆነ ብቻ ብለዋል ሲል አውሎ ሚዲያ ዘግቧል።

ወይዘሮ ኬርያ አክለውም እኔ መመስከር ካለብኝ የምመሰክረዉ መንግስት በህዝብና ሀገር ላይ እየፈጸመ ያለውን ክህደት እና ወንጀል ከሆነ ብቻ ነዉ፤ ፍርዱ ቤቱ እንዲያቅልኝ የምፈልገዉ ብቻዬን እስካሁን በአንድ ክፍል ታስሬ ብመሰከርም ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንወስድሻለን፤ ፍትህ ታገኛለሽ በማለትና በማስፈራራት፤ ቪድዮ በመቅረጽ መብቴ ተጥሶ ነዉ ያለሁት ማለታቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img