Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአሜሪካ የቪዛ ክልከላ ጉዳይ ከሕዳሴው ግድብ ሊገናኝ እንደሚችል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 17፣ 2013 ― የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ ከህዳሴው ግድቡ ጋር ሊገናኝ የሚችልባቸው መንገዶች ሊኖሩ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

አሜሪካ በቅርቡ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕተኛ አድርጋ የሾመቻቸው ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በነበሩበት ወቅት ስለ ግድቡ ድርድር ጉዳይ አንስተው እንደነበር ያስታወሱት ዲና ሙፍቲ፣ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኩል ግልጽ አቋሟን እንደተቀመጠላቸው ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ ከአሁን ቀደም ግድቡን በተመለከተ ጫን ያለ የተደራደሩ አቋም እንደነበራት የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህም ኢትዮጵያ በዋሽንግተን ሲካሄድ ከነበረው የድርድር ሂደት አፈንግጣ መውጣቷ አይዘነጋም፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በአጠቃላይ አሜሪካ አሁን ያደረገችውን ‹‹ክልከላ›› ለራሷም እንደማይጠቅማት የተናገሩ ሲሆን፣ ‹‹ለዚህ የሚያበቃ ምንም ምክንያት›› አለመኖሩን በመግለጽ፣ ‹‹የአሜሪካ ፍላጐት በእኛ (በኢትዮጵያ) ፍላጎት ኪሳራ ላይ መሆን የለበትም›› ሲሉም አክለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img