Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ትግራይ ላይ መርዛማ ጋዝ ተጠቅሟል መባሉን መከላከያ ውሸት ነው አለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 17፣ 2013 ― ከትላንት በስትያ ግንቦት 15፣ 2013 በታተመው የእንግሊዙ ዘ ቴሌግራፍ ጋዜጣ ላይ በትግራይ ክልል ከአንድ ወር በፊት የመርዛማ ጋዝ ጥቃት ተፈጽሟል በሚል ዘገባ መውጣቱን የመከላከያ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል ጌትነት አዳነ ውሸት ነው ብለውታል፡፡

ዘ ቴሌግራፍ በዘገባው ከትግራይ ክልል አገኝኋቸው ያላቸውን ተጎጂዎች እንዲሁም በኬሚካሉ ምክንያት ሰውነቷን የተቃጠለች የ13 ዓመት ታዳጊ ታሪክ ይዞ የወጣ ሲሆን፣ የደረሰው ጥቃት የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦር በሲቪል ዜጎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ተቀጣጣይ የሆነ መሳሪያ ተጠቅሞ ሊሆን ይችላል ሲል ገልጾ ነበር፡፡

ሆኖም ተፈፀመ የተባለውን የመርዛማ ጋዝ ጥቃት ሕዝብ ግንኙነቱ ‹‹ሊደረግ ቀርቶ ሊታሰብ የማይችል ነው›› ሲሉ መግለጻቸውን መከላከያ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላላ አስነብቧል፡፡

የሕዝብ ግንኑነቱ ውሸት ነው ላሉት ዘገባ ወሬውን በመንዛት ሕወሃትን ወንጅለዋል፡፡ አክለውም ድርጅቱ ከዚህ ቀደምም ቢሆን በመከላከያ ሠራዊት ላይ የትግራይን ሕዝብ እየጨፈጨፈ ነው ማለቱን፣ ሴቶች ተደፍረዋል ማለቱን፣ መከላከያ እርዳታ መከልከሉን፣ ገበሬው እርሻ እንዳያርስ ማድረጉን እና ሌሎችንም ወሬዎች አሰራጭቷል ብለውታል፡፡

ይህ ዐይነቱን ‹‹የበሬ ወለደ ውሸት›› ነው ያሉትን የሚያስተናግዱ ሚዲያዎችንም ‹‹አንድም ለቆየ ዓላማቸው፤ በሌላም ኢትዮጵያ በተዘረፈችው ዶላር የተገዙ ነጭ ሸብር ፈጣሪዎች›› እንደሆኑ ኮለኔል ጌትነት አስረድተዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያ የጅምላ ጨራሽ ጦር መሳሪያዎችን ያለመጠቀምና ያለማስተላለፍ ዓለም አቀፍ ስምምነትን የፈረመች እና ያፀደቀች ቀዳሚ ሃገር መሆኗንም አንስተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img