Saturday, November 23, 2024
spot_img

የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት ኢትዮጵያ እና ሱዳንን የማሸማገል እቅዴን ትቼዋለሁ ማለቷ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 17፣ 2013 ― ለረዥም ጊዜያት የቆየውን የኢትዮጵያን እና ሱዳንን የድንበር ውዝግብ የማሸማገል እቅድ እንደነበራት የተነገረላት የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት የማሸማገል እቅዴን ትቼዋለሁ ማለቷን መቀመጫውን ሳዑዲ ያደፈረገው አሽረቅ የዜና ተቋምን ዋቢ አድርጎ ዴይሊ ሰባህ ዘግቧል፡፡

የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት አሁን ትቼዋለሁ ያለችው የማሸማገል እቅድ ከሱዳን ባለሥልጣናት በኩል አስተያየት የተሰጠበት ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ በይፋ ያለችው ነገር አልተሰማም፡

ከሱዳን በኩል በተለይ የሽግግር ምክር ቤት አባል የሆኑት ማሊክ አጋር አገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ውዝግብ ለማርገብ የቀረበውን የሽምግልና ሐሳብ እንደማይቀበሉት በይፋ ማሳወቃቸውን የሱዳን ጋዜጦች በወቅቱ ዘግበው ነበር፡፡

የሽግግር ምክር ቤት አባሉ በወቅቱ የዐረብ ኤሜሬቶችን ሐሳብ ላለመቀበላቸው ከኢትዮጵያ ጋር ባለው የድንበር ውዝግብ አወዛጋቢውን የአል ፈሻቃ መሬት የማካፈል እቅድ እንዳላት ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ የቀረበውን ይህንኑ የሽምግልና ሐሳብ ከዚህ ቀደም አገራቸው መቀበሏን የሱዳን መንግሥን ቃል አቀባይ ሐምዛ ባሉል ተናግረው ነበር፡፡

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ መሬት መጠጋቱን ተከትሎ ለረዥም ዓመታት ሲያነታርካቸው የቆየው የድንበር ውዝግብ ዳግም አገርሽቶ ውዝግብ ውስጥ ከገቡ ስድስት ወራት አልፎታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img