Sunday, September 22, 2024
spot_img

የመንግሥት ባለሥልጣናት ቅንጡ ኑሯቸውን እንዲቀይሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አሳሰቡ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 17፣ 2013 ― እውቁ የቀድሞ ፖለቲከኛ እና የወቅቱ የኢሳት ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ መጣሏን ተከትሎ የመንግሥት ባለሥልጣናት ቅንጡ ኑኗቸውን እንዲያስተካክሉ አሳስበዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው በሚመሩት ኢሳት ላይ ቀርበው እንደተናገሩት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት ‹‹ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀጥ ብለው››፣ ሴሚናር ወርክ ሾፕ የሚያዘጋጁትን በመተው እንዲሁም ‹‹በዲዛይነር የሚለብሱትን አቁመው›› ወጪ መቀነስ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የአሜሪካን የፋይናንስ ማእቀብ ለመሸፈን ‹‹አማራጭ አገር መፈለግ›› ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን፣ ባለፉት 28 ዓመታት ከአሜሪካ ጋር ከነበረው ‹‹የልማት አጋርነት ምን አተረፍን ተብሎ መጠየቅ አለበት›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቅርብ ሰው እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሳምንት በፊት የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የአገሪቱን ባንዲራ ማቃጠል የሚል ሐሳብ አንጸባርቀው መነጋገሪያ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img