Wednesday, October 9, 2024
spot_img

የአሜሪካ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ ጨረታ ካሸነፉት መካከል በሆነው ቮዳፎን ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 16፣ 2013 ― የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ የጣለው ማዕቀብ ወደ ኢትዮጵያ ቴሌኮይ ገበያ ለመግባት ጨረታ ካሸነፉት መካከል በሆነው ቮዳፎን ላይ ችግር ሊፈጥር የሚችል መሆኑን ብሉምበርግ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች ተረድቻለሁ ብሏል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ቮዳፎን ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኮርፖሬሽን 500 ሚሊዮን ዶላር ለመበደር ከስምምነት ላይ ደርሶ ነበር።

ሆኖም ይህ ስምምነት አሜሪካ ከፋይናንስ ጋር የተገናኘ ማዕቀብ በመጣሏ ኩባንያው በቀጣይ የኩባንያው አካሄድ ላይ ከባይደን አስተዳደር ትዕዛዝ እንደሚጠብቅ ነው የተነገረው።

በጉዳዩ ላይ ኩባንያው አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img