Wednesday, October 9, 2024
spot_img

አቶ እስክንድር ነጋ በምርጫ እጩነት እንዲመዘገቡ ፍርድ ቤት መወሰኑን ፓርቲያቸው አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 16፣ 2013 ― በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ በቀጣይ ወር ለሚካሄደው ምርጫ በእጩነት እንዲመዘገቡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ መስጠቱን ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከሊቀመንበሩ በተጨማሪ ሌሎች ታሳሪዎችን ማለትምአስቴር ስዩም፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌም በመጪው ምርጫ በዕጩነት እንዲመዘገቡ መወሰኑም ጨምሮ ተገልጧል፡፡

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያለው ነገር የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img