Friday, November 22, 2024
spot_img

ግጭት ያስተናገደው የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ትምህርት ለማስጀምር መቸገሩን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 16፣ 2013 ― ባሳለፍነው መጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ግጭት ያስተናገደው በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ትምህርት ለማስጀምር መቸገሩን አስታውቋል፡፡

የወረዳው የኮሚኒኬሽን ቢሮ የትምህርት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊውን አቶ አሕመድ ዐብዱን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፣ በአሁኑ ወቅት በኮማንድ ፖስት ስር በሚገኘው ወረዳ ውስጥ ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች መካከል 38 የሚሆኑ አንደኛ ደረጃ እና በከፊል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስራ የጀመሩ ቢሆንም፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን ተፈናቃዮችን በመጠለያነት እያገለገሉ ያሉ ትምህርት ቤቶች በመኖራቸው፣ በጦርነቱ ወቅት ሙሉ ለሙሉ የወደሙ ት/ቤቶች በመኖራቸው እና በግጭቱ ምክንያት የአካባቢው ማኅበረሰብ ከት/ ቤቱ ርቀው በመሄዳቸው ምክንያት ትምህርት ለማስጀመር እክል ፈጥሯል፡፡

በሌላ በኩል ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እና ክልል አቀፍ የ8 ክፍል ፈተና ለማስፈተን በሁሉም ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ትምህርት እየሰጡ እንደሚገኙ ምክትል ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ካጋጠማቸው ችግር ውጪ በአሁኑ ሰአት አካባቢው ሰላም የሰፈነበትና የተረጋጋ በመሆኑ ተማሪዎች ያለምንም ፍረሃት ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል እንዳለባቸውም አያይዘው ገልጸዋል፡፡

ፎቶ፡ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የትምህርት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊው አቶ አሕመድ ዐብዱ
የፎቶ ምንጭ፡ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img