Wednesday, October 9, 2024
spot_img

የብልየምሥራቅ ትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ሃገረ ስብከት በክልሉ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 16፣ 2013 ― የምሥራቅ ትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ሃገረ ስብከት በትግራይ ክልል ተፈጽሟል ያለችውን የንጹሐን ጥቃት አውግዟል፡፡

ሃገረ ስብከቱ በመግለጫው በክልሉ በተፈጸመ ጥቃት ሕይወታቸውን አጥተዋል ያላቸውን ዘርዝሯል፡፡ በዚሁ መሠረት 6 መነኮሳት፣ 51 ቀሳውስት፣ 2 የአብነት መምህራን፣ 17ዲያቆናት፣ 24 የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን እና 1 ሺሕ 85 ምዕመናን ሕይወታቸውን አጥተዋል ብሏል፡፡

በተጨማሪም በኅዳር ወር 21ኛው ቀን በደንገላት ማርያም ቤተ ክርስትያን፣ ታኅሣሥ 27 በጉዕተሎ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስትያን እና ታኅሣሥ 28 እና 29 ደግሞ በፍረ ዳሹም ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስትያን ተጨፍጭፈዋል ያላቸውን ሰዎ ች የዘረዘረው መግለጫው፣ በተመሳሳይ ደብረዳሞ ገዳም ላይ ደርሷል ያለውን ውድመትና የተዘረፉ ንዋያተ ቅድሳትን ጠቅሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img