Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ሦስት የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በአስገድዶ መድፈር ተከሰው እንደተፈረደባቸው ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 14፣ 2013 ― የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሦስት የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በአስገድዶ መድፈር እንዲሁም ሌላ አንድ ወታደር ደግሞ ሲቪል ዜጎችን በመግደል እንደተፈረደባቸው በትላንትናው እለት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በትግራይ ክልል በንጹሐን ግድያና በጾታ ጥቃቶች ላይ ትኩረት በማድረግ አካሄድኩት ባለው ምርመራ፣ የወታደራዊ ግዴታ በሌለበት ወቅት በግድያ የተጠረጠሩ 28 የአገር መከላከያ ወታደሮች ላይ ክስ መመስረቱን ጨምሮ ገልጧል፡፡

በሌላ በኩል ጾታዊ ጥቃትና አስገድዶ መድፈር የፈጸሙ 25 ወታደሮችም ክስ ተመስርቶባቸዋል ያለው ዐቃቤ ሕግ፣ በክሶቹ ላይ በአጭር ጊዜ ፍርድ እንደሚሰጥ ነው የገለጸው፡፡

በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የንጹሐን ግድያና ፆታዊ ጥቃት ጨምሮ የሰብአዊ መብት ጥሰት በግጭቱ ተሳታፊ ኃይሎች መፈጸሙን በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና በተለያዩ የዓለም አቀፍ የመብት ድርጅቶች ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img