Tuesday, October 8, 2024
spot_img

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የፋይናንስ ማእቀብ ለማጣል እቅድ እንዳላት ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 14፣ 2013 ― የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የፋይናንስ ማእቀብ የመጣል እቅድ እንዳለው ብሉምበርግ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሁለት ግለሰቦች ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቧል፡፡

የዜና ተቋሙ ጉዳዩን ለማረጋገጥ ለአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት እና አዲስ አበባ ለሚገኘው የአገሪቱ ኤምባሲ ኢሜል ብልክም ምላሽ አልሰጡኝም ብሏል፡፡ በተጨማሪም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቃል አቀባይ ቢልለኔ ሥዩም የላኩት የጽሑፍ መልእክት ምላሽ አላገኘም ሲል አክሏል፡፡

የባይደን አስተዳደር በተመሳሳይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እቀባ የመጣል እቅድ እንዳለው ፎሬን ፖሊሲ መጽሔት ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ባለሥልጣናት ነግረውኛል ብሎ ትላንት ምሽት መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

ለእቀባው እቅድ መነሻ የሆነው በትግራይ ክልል በንፁሐን ላይ ተፈጽሟል ያለው የጭካኔ ተግባር መሆኑ ነው የተነገረው፡፡ በጉዳዩ ላይ ከሁለቱም መንግሥታት በኩል በይፋ የተባለ ነገር የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img