Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የናይጄሪያ የጦር ኃላፊ በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 14፣ 2013 ― የናይጄሪያ የጦር ኃላፊ ጄኔራል ኢብራሂም አታሂሩ በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

ኃላፊው በሰሜን ምዕራብ በምትገኘው ካዱንጋ ግዛት የተሳፈሩበት አውሮፕላን ተከስክሶ መሞታቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በአደጋው ከኃላፊ ተጨማሪ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት አስር ወታደሮችና እንዲሁም የአውሮፕላኑ ሰራተኞችም ሞተዋል የተባለ ሲሆን፣ አውሮፕላኑ መጥፎ በተባለ አየር ሁኔታ ለማረፍ ሲሞክር መከስከሱን ጦሩ ገልጿል።

አደጋውን ተከትሎ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ በኃላፊው ሞት ‹‹‹ጥልቅ ኃዘን ተሰምቶኛል›› ብለዋል፡፡

የ54 አመቱ ጄኔራል ኢብራሂም አታሂሩ የነበሩበትን ሹመት ያገኙት በያዝነው አመት ጥር ወር ላይ እንደሆነና ከፍተኛ ሹመትም እንደነበር ተነግሮለታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img