Saturday, November 23, 2024
spot_img

የኤርትራ ጦር ኢትዮጵያን ለማገዝ እንዳልገባ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 14፣ 2013 ― በጥቅምት ወር የመጨረሻ ቀናት በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በመግባት እስካሁንም ድረስ በኢትዮጵያ መሬት ላይ እንደሚገኝ የሚነገረው የኤርትራ ጦር በወቅቱ ወደ ኢትዮጵያ የዘለቀው የኢትዮጵያን ጦር ለማገዝ ሳይሆን እራሱን ለመከላከል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዐሕመድ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተናግረዋል፡፡

ዲያቆን ዳንኤል ኢትዮ ቲዩብ ከተባለ የኦንላይን ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ በጦርነቱ ‹‹የኢትዮጵያ ጦር ለራሱ በቂ ነው›› ያሉ ሲሆን፣ ከኤርትራ ጦር ጋር ‹‹ግንባር ገጥመው›› እንዳልታገሉም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ መሬት ላይ የሚገኙት የኤርትራ ወታደሮችን በተመለከተ በጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ ለቅቀው እንደሚወጡ ቢነገርም፣ አሁንም በሚገኙበት የትግራይ ክልል የሰብአዊ አቅርቦት እንዲስተጓጎል እያደረጉ እንደሚገኙ የሚያመለክቱ ሪፖርቶች ወጥተዋል፡፡

በሌላ በኩል በዚሁ ቆይታቸው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በነበሩ ጊዜያት ‹‹ጦርነት ብሎ ቅዱስ ስለሌለ›› የሽምግልና ጥረት መደረጉን ያነሱ ሲሆን፣ ይህንኑ ሽምግልና በተመለከተ እርሳቸው እንደ ግለሰብም እንደ ቡድንም ‹‹በልኬ ስለሠራሁ የሚጸጽተኝ ነገር የለም›› ሲሉ ተደምጠዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img