Thursday, November 21, 2024
spot_img

ሰበር፡ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እቀባ የመጣል እቅድ እንዳለው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 13፣ 2013 ― የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እቀባ የመጣል እቅድ እንዳለው ተሰምቷል።

የባይደን አስተዳደር ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተጨማሪ በኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ ለመጣል ላቀደው የቪዛ እቀባ እቅዱ መነሻ የሆነው በትግራይ ክልል በንፁሐን ላይ ተፈጽሟል ያለው የጭካኔ ተግባር መሆኑን ፎሬን ፖሊሲ መጽሔት ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ባለሥልጣናት ተናግረዋል ብሎ ዘግቧል።

መጽሔቱ በዘገባው የባይደን አስተዳደር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር የትግራይ ክልል ጦርነትን በያዘበት መንገድ ደስተኛ አለመሆኑን አስፍሯል።

የአሜሪካ መንግሥት በትግራይ ክልል ጦርነት መከሰቱን ተከትሎ በክልሉ ከሚገኙ የኤርትራ ወታደሮች፣ ከሰብአዊ ርዳታ አቅርቦት፣ ከሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጋር በተገናኙ ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ሲያወጣ መሰንበቱ የሚታወቅ ነው።

በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንቶንዮ ብሊንክን በኩል ከቀናት በፊት የወጣውን የአሜሪካ መንግሥት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት መግለጫውን ሉአላዊነትን የሚጋፋ ነው ማለቱ የሚታወስ ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img