Sunday, October 6, 2024
spot_img

Update

UPDATE: በትላንትናው እለት ወደ አገሩ የተባረረው የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢ ሳይመን ማርክስን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ በሰጡት ማብራሪያ ጋዜጠኛው ያለ ዘጋቢነት ሥራ ፈቃድ ሀገር ውስጥ መቆየት እንደማይችል በበመግለጽ፣ «እዚህ ያለኸው ለሥራ ነው። ፈቃድ ካለህ ትቆያለህ። ፈቃድህ ከተቀማ ግን ኃላፊነት ያለው አካል ወደመጣህበት ይመልስሃል» ማለታቸውን የዜና ወኪሉ አስነብቧል።

ከወር በፊት ፈቃዱ የተቀማው ጋዜጠኛ ሳይመን ማርክስ፣ በባለሥልጣኑ ርምጃ የተወሰደበት ትግራይ ክልል አቅንቶ የሠራው ዘገባ ሚዛናዊነት ጎድሎታል በሚል እንደነበር መነገሩ አይዘነጋም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img