Tuesday, November 26, 2024
spot_img

ሱዳን ከአሜሪካ የሽብር ደጋፊ አገራት ዝርዝር ውስጥ እንድትወጣ ተደረገ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 13፣ 2013 ― አሜሪካ ሱዳንን ለዓመታት ካቆየቻት የሽብር ተግባራትን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር ውስጥ እንድትወጣ የማድረግ ሂደትን ማጠናቀቋ ተነግሯል።

በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የተዘጋጀ ሰነድ ሱዳን ከአሜሪካ የሽብር ደጋፊ አገራት ዝርዝር ውስጥ እንድትወጣ የማድረጉ ሥራ መከናወኑን አመልክቷል።

ሱዳን የሽብር ተግባራትን ከሚደግፉ የአገራት ዝርዝር ውስጥ እንድትወጣ በይፋ ውሳኔ ላይ የተደረሰው ባለፈው ታኅሣሥ ወር ላይ ሲሆን፣ የአገሪቱን ስም ሙሉ ለሙሉ ነጻ ለማድረግ የወራት ጊዜን ፈልጓል።

በዚህ መሠረት አስፈላጊው ሂደት ተጠናቆ ሱዳን ከአሜሪካ የሽብር ዝርዝር ውስጥ መውጣቷ ተግባራዊ የሆነው በዚህ ሳምንት ከዕለተ ረቡዕ ጀምሮ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

ይህ ሱዳንን ለ27 ዓመታት በሽብር ደጋፊነት ያቆያት ውሳኔን ተከትሎ በአሜሪካ የተጣሉባት ማዕቀቦች በኢኮኖሚዋ ላይ ከባድ ጉዳት ማስከተሉን ዘገባው አስታውሷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img