Tuesday, October 8, 2024
spot_img

በትግራይ ደቡባዊ ዞን የተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 13፣ 2013 ― በትግራይ ደቡባዊ ዞን ትምህርት ለማስጀመር የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የዞኑ ማኅበራዊ ጉዳይ መመሪያ አስታውቋል፡፡

የመምሪያው አስተባባሪ አቶ አብርሃ ደሳለው እንደገለጹት፣ የተማሪዎች ምዝገባ የተጀመረው በአንደኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነው።

ምዝገባው ከተጀመረባቸው የዞኑ አካባቢዎች መካከል መኾኒ እና አዲሸሁ ከተሞች እንደሚገኙበት ጠቅሰው፤ ምዝገባውን በማጠናቀቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትምህርት እንደሚጀመር ኢዜአ ዘግቧል።

ተማሪዎች ትምህርት በሚጀምሩበት ወቅት ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ 40 ሺሕ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲሁም ሳኒታይዘር ዝግጁ ተደርጓል ብለዋል።

በማይጨውና ሌሎች የዞኑ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አቶ አብርሃ ጠቁመዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img