Sunday, September 22, 2024
spot_img

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የአሜሪካ ባንዲራ የማቃጠል እቅዳቸውን እንደተዉት ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 13፣ 2013 ― እውቁ የቀድሞ የፖለቲካ ሰው እና በአሁኑ ወቅት የኢሳት ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከቀናት በፊት የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ላወጣው መግለጫ ምላሽ ‹‹በአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ባንዲራዋን ማቃጠል›› አለብን የሚል ሐሳባቸውን መለወጣቸውን ለሚመሩት ኢሳት ተናግረዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ‹‹የኔን ንዴት ባንዲራ አቃጥዬ መግለጽ መብት ቢሆንም፣ ያን ማድረግ ግን ሌሎችን ሊያስከፋ ይችላል፤ አሜሪካ ባልጓል ብለን ማቃጠል የለብንም፣ እኛ እንደነሱ ባልገን የአሜሪካን ባንዲራ አናቃጥልም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ‹‹ሲጠግቡ ጠግባችኋል ማለት አለብን›› ያሉት አቶ አንዳርጋቸው፣ በሌላ ጎን ‹‹እስካሁን ከጎናችን ነበሩ›› ላሏቸው ሩሲያ፣ ሕንድ እና ቻይና የምሥጋና ደብዳቤ እንደሚደርሳቸው ገልጸዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የአሜሪካን መግለጫ ተከትሎ ያነሱትን የባንዲራ ማቃጠል ውጥን ሰምቻለሁ ያለው አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በዚሁ ሰበብ ዛሬ እለት አገልግሎት እንደማይሰጥ ቀድሞ ማሳሰቡ አይዘነጋም፡፡

በሌላ በኩል አቶ አንዳርጋቸው አብረውት መግለጫ የሰጡት ብሄራዊ ክብር ለህብር የተሰኘ ማህበር በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ነው ላለው ጫና ‹‹እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ›› በሚል መሪ ሐሳብ የተቃውሞ እንቀስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ ዋልታ ዘግቧል፡፡

የብሄራዊ ክብር ለህብር አስተባባሪ አብይ ታደለ ሁሉም ለሀገሩ ያገባኛል የሚል እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ገልጸው፣ ከሲቪል ማህበራት፣ ከኃይማኖት ተቋማት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን ፍሬያማ የሆነ የተቃውሞ ደብዳቤ ወደ ኤምባሲዎች ለማስገባት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ኤምባሲዎች ዛሬ ባለመስራታቸው አልተሳካም ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img