Tuesday, October 8, 2024
spot_img

በጎንደር ከተማ ከመቃብር ሥፍራ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ ችግር ለወጣቶች እስር ሰበብ ሆነ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 13፣ 2013 ― በጎንደር ከተማ ከአንድ ወር በፊት የሞቱ ሙስሊሞችን ለመቅበር ሕዝበ ሙስሊሙ በቦታው ሲገኝ ‹‹የሞተው የኛ ሰው ነው ገድላችሁት ነው›› በሚል ሁከት ባስነሱ የሌላ እምነት ተከታይ ግለሰቦች አማካኝነት አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ተነግሯል፡፡

ኋላም በወቅቱ የተባለው ወሬ ፈጽሞ ሐሰት መሆኑ እንደነበርና የቤተ ክህነት አመራሮችም በተፈጠረው ተግባር ይቅርታ ጠይቀው በመግባባት ታልፎ ነበር ነው የተባለው፡፡

ሐሩን ሚዲያ እንደዘገበው ከሆነ ከዚህ ክስተት በኋላ ባለፈው ወር በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የጾም ወቅት በሆነው የረመዳን ወር የመጀመሪያ ቀናት ላይ አለመግባባቱ አገርሽቶ በተፈጠረው ችግር ሁለት ወንድማማቾች ‹‹አላሁ አክበር›› ብላችኋል በሚል ክስ በእስር ከቆዩ በኃላ ባለፈው ሳምንት ከተከበረው የዒድ አልፈጥር በዓል አንድ ቀን ቀድሞ በገንዘብ ዋስ የተለቀቁ ቢሆንም፣ በዓሉ ካለፈ በኃላ ግን ተመልስው ታስረዋል፡፡

ለእስር የተዳረጉት ጡሃ ኑርሑሴን እና መሐመድ ኑርሑሴን የተባሉት ወጣቶች የክስ ወረቀት እንደሚያመለክተው ፖሊስ የመሠረተባቸው ክስ ‹‹አላሁ አክበር በማለት የክርስትያንና የሙስሊም ግጭት እንነሳሳ ሁከት በመፍጠር›› እንዲሁም ‹‹በሃይማኖት ሰላም እና ስሜት መንካት›› የሚል ነው፡፡

ወጣቶቹ በዋስትና ከተለቀቁ በኋላ ዳግም ለምን እንደታሰሩ ምንም የተባ ነገር የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img