Monday, November 25, 2024
spot_img

መንግሥት የኒውዮርክ ታይምስን ዘጋቢ ከአገር አባረረ

ሲፒጄ የጋዜጠኛውን መባረር ኮንኗል

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 13፣ 2013 ― ባለፈው ወር በኢትዮጵያ የዘገባ ፍቃዱ እንደታገደበት ተነግሮ የነበረው የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢ ሳይመን ማርክስ በትላንትናው እለት ከአገር እንደተባረረ ታውቋል፡፡ ይህንኑ ቀጣሪው ኒውዮርክ ታይምስ የዘገበ ሲሆን፣ ጋዜጠኛ ሳይመን ማርክስም በትዊተር ገጹ ላይ አረጋግጧል፡፡

እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ከሆነ ዘጋቢው ለስብሳባ ትፈለጋለህ ተብሎ ተወስዶ በዚያው ወደ አገሩ እንዲሸኝ ተደርጓል፡፡

ሳይመን ማርክስ መባረሩን ተከትሎ ባሠፈረው መረጃ የኢሚግሬሽን ሠራተኞች ወደ መኖሪያ ቤት ተመልሶ እቃዎቹን ለመሰብሰብ እና ልጁን ለመሠናበት እድል እንዳልሰጡት የገለጸ ቢሆንም፣ አንድ ቀን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ እንደምመጣ ተስፋ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

የጋዜጠኛውን መባረር ተከትሎ የታይምስ ዓለም አቀፍ ምክትል ማኔጂንግ ኤዲተር ማይክል ስላክማን የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኛውን ‹‹እንደ ወንጀለኛ የያዘበት መንገድ›› አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄም የጋዜጠኛውን ከኢትዮጵያ መባረር ኮንኗል፡፡

ከአገር የተባረረው የአየርላንድ ዜግነት ያለው ሳይመን ማርክስ፣ ቀድሞ የዘገባ ፍቃዱ ተሰርዞ የነበረው ወደ ትግራይ አቅንቶ ዘገባ ካስነበበ በኋላ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፣ ፍቃዱን የሰረዘው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥጣን ጋዜጠኛው የሠራው ዘገባ ‹‹ሚዛናዊነት ይጎድለዋል›› የሚል ምክንያት አስቀምጦ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img