Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ የአሜሪካ መንግሥት ከሰሞኑ ያወጣውን መግለጫ አወገዘ

[et_pb_section admin_label=”section”] [et_pb_row admin_label=”row”] [et_pb_column type=”4_4″][et_pb_text admin_label=”Text”]

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 12፣ 2013 ― የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጌታ ፓሲ በጻፈው ደብዳቤ በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሰሞኑን የተሰጠው መግለጫ ኢፍትሐዊና በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት እና ሉዓላዊነትን ያለመጣስ የተባበሩት መንግሥታት መርህን የሚቃረን ነው ብሏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሕጋዊ ምርመራዎች በተገቢው አካላት ከመከናወናቸው በፊት ለሕወሃት ቅሪቶች የተሳሳተ መረጃ እውቅና መስጠታቸው እንዳሳዘነው መማክርቱ ገልጿል፡፡ ምንም እንኳን ሚኒስትሩ ለሰብዓዊ መብት ሁኔታዎች መሻሻል ያሳዩትን ተቆርቋሪነት እና ተሳትፎ መማክርቱ ቢያደንቅም፣ የተወሰደው አቋም በመሬት ላይ ያለውን እውነታ በትክክል የማይገልጽ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

የሰብዓዊ ዕርዳታ በአግባቡ እንይዳረስ እክል በመፍጠር ረገድ ቀጥተኛ ተጠያቂው ሕወሃት ሆኖ እያለ የሚኒስትሩ መግለጫ በክልሉ ያለውን ነባራዊ እውነታ የማይገልጽ፣ ትክክለኛነት እና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ሲል መማክርቱ አውግዟል፡፡

ስለ አማራ ልዩ ኃይል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ የተነሳው በአካባቢው ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር በፍጹም የሚቃረን ነው ብሏል ጉባኤው፡፡

የወልቃይት ጠገዴ እና የሰቲት ሁመራ አስተዳደር ዞንን ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ ማሳሰብ የሕዝቡን ፍላጎት በግልፅ የሚፃረር እና ለ30 ዓመታት ያህል ህወሃት በአካባቢው ሲፈጽመው የነበረውን የዘር ማጥፋት እንዲደገም የሚደረግ ሙከራ ነው ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተመርምሮ ሪፖርት የተደረገውን የማይካድራ የዘር ማጥፋት ወንጀልን አይነት ጥፋት ሕዝቡን ለሁለተኛ ዙር አሳልፎ መስጠት መሆኑን መማክርቱ በጻፈው ደብዳቤ አመላክቷል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና የወልቃይት ጠገዴና የሰቲት ሁመራ አስተዳደር ዞን ላይ ያለውን አቋም እንዲያጤነው የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ አሳስቧል፡፡

[/et_pb_text][/et_pb_column] [/et_pb_row] [/et_pb_section]
ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img