Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጭነት ምዝገባ ጊዜ ማራዘሙን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 11፣ 2013 ― የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባን በበይነ መረብ ሲያካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለተማሪዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ መሰጠት እንዳለበት መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ቦርዱ የተቋማቱ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ሲያደርጉ እንደቆዩት እስከ ግንቦት 17፣ 2013 ድረስ ባለው ጊዜ https://www.ovrs.gov.et በኩል በሚገኘው የመመዝገቢያ ሊንክ እንዲመዘገቡ ብሏል፡፡

ምርጫ ቦርድ ይኸው እንዲከወን የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች በማስታወስ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ እንድታደርጉ ሲል ትብብር ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img