Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሥራቸውን ለቀቁ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 10፣ 2013 ― የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ ቁልፍ የመንግስት ተቋም የሆነውን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን በኃላፊነት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ኤባ አባተ ስራቸውን መልቀቃቸው ታውቋል።

ዶ/ር ኤባ ስራቸውን የለቀቁት “በገዛ ፍቃዳቸው” እንደሆነ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር የተባለው ድረ ገጽ ገልፀውልኛል ያለ ሲሆን፣ ለመልቀቃቸው ምክንያት ነው ያሉትን ግን አለመናገራቸው ተመላክቷል።

ከጥር 2009 ጀምሮ ላለፉት አራት ዓመታት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት ዶ/ር ኤባ፣ የስራ መልቀቂያቸውን ያስገቡት ባለፈው ሳምንት መሆኑንም ዘገባው አመልክቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img