Sunday, September 22, 2024
spot_img

የቤንሻንጉል ክልል መንግስትና የክልሉ ታጣቂ ቡድን የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 10፣ 2013 ― በመተከል ዞን እየተከሰተ ያለውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት መፍትሄ ለመስጠት በክልሉ መንግስትና በታጣቂ ቡድኑ መካከል የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ተካሄዷል።

በዚሁ ስምምነት ታጣቂው ሃይል አቅምና የትምህርት ደረጃውን በማየት በክልል ደረጃ 2፣ በዞን ደረጃ 3 እና በወረዳ ደረጃ ደግሞ 4 የሃላፊነት ቦታ እንዲያገኙ ማድረግ እንዲሁም የከተማ የቤት መስሪያ ቦታ፣ የገጠር የእርሻ መሬት እያዲያገኙ ተብሏል።

በተጨማሪም ሴቶችን አካታች ያደረገ በተለያዩ ማህበራት እንዲደራጁ ማስቻል፣ በተማሩበት የሙያ መስክ እንዲመደቡ ማድረግ እና ከአሁን በፊት ልምድ ያላቸውን ሰዎች በክልሉ ውስጥ ባሉ የጸጥታ መዋቅሮች መመደብ እና የብድር አገልግሎት መስጠት የሚሉትም ተካተዋል።

የስምምነት ሰነዱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በአቶ አሻድሊ ሐሰን እና በታጣቂ ቡድኑ ተወካይ በአቶ ጀግናማው ማንግዋ ተፈርሟል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img