Friday, November 22, 2024
spot_img

የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት በኢትዮጵያ የረሃብ አደጋ ስጋት መኖሩን አመለከተ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 10፣ 2013 ― የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት ዩኤስ አይዲ በኢትዮጵያ የረሃብ ስጋት መኖሩን አመለከተ፡፡ ይህንኑ የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስአይዲ) መሪ እና የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በነበራቸው የጋራ ውይይት ላይ ስለመናገራቸው ድርጅቱ በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል።

የዩኤስአይዲ መሪ ሳማንታ ፓወር ከዩኬው የውጭ፣ የኮመን ዌልዝና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶሜኔክ ራብ ጋር በበይነ መረብ አማካይነት ሲወያዩ በኢትዮጵያና በየመን እየጨመረ ነው ስላሉት የረሃብ ስጋት መወያየታቸውን ነው ዩኤስአይዲ ያስታወቀው፡፡

‹‹እንደ በኢትዮጵያና የመን ባሉ አገራት እየጨመረ ስለመጣው የረሃብ ስጋት መክረዋል›› ከማለት ውጪ በየትኛው የአገሪቱ ክፍል የረሃብ አደጋ ስጋት እንዳለ ያለው ነገር ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

በትግራይ ክልል ‹‹በርካቶች በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ›› ባለፈው ጥር ወር አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሠራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ ሰፍሮ መገኘቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img