አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 10፣ 2013 ― የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ የገጠር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እቅድ ስላለኝ የኢንቨስትመት መሬቶችን ለአንድ የምርት ዘመን ለማከራየት እፈልጋለሁ ሲል አስታውቋል፡፡
ክልሉ ባወጣው ማስታወቂያ ከአሁን ቀደም መሬት ወስደው እያለሙ የነበሩ በማንነታቸው በአካባቢው በነበረው ፖለቲካዊ ችግር ተፈናቅለው የነበሩ አልሚ ባለሐብቶች እና በክልሉ በፀጥታ ችግር ምክንት መሬታቸውን ማልማት ያልቻሉ ባለሐብቶች ተጋብዘዋል፡፡
የአማራ ክልል አሁን ለባለሐብቶች በኢንቨስትመንት ለማከራየት ያወጣቸው መሬቶች ከዚህ ቀደም ከትግራይ ክልል ጋር ሲያነታርክ የቆየ መሆኑ ይነገራል፡፡