Sunday, October 6, 2024
spot_img

በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ አሰቃቂ መሆኑን ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 10፣ 2013 ― የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ አሰቃቂ መሆኑን በትላንትናው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ አምስት ሚሊዮን ያህል ሰዎች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጹት ዶክተር ቴድሮስ፣ ድጋፋ ያላገኙ ሰዎች በምግብ እጥረት ሰበብ ረሀብ በርትቶባቸው በርካቶች እየሞቱ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በዚሁ መግለጫ ላይ በትግራይ ክልል በዜጎች ላይ ይደርሳል ያሉትን ግድያ እና ጾታዊ ጥቃቶን አንስተው የኮነኑት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ይፈጸማል ያሉት የሴቶች አስገድዶ መደፈር ከቁጥጥር ውጭ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል በመግለጫው ወቅት በትግራይ ክልል ያለውን የኮሮና ቫይረስ የሥርጭት ሁኔታ የተጠየቁ ቢሆንም፣ ዶክተር ቴድሮስ ግን ከሌሎች ነገሮች አንጻር አንገብጋቢ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img