Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የባይቶና ፓርቲ አመራሩ አቶ ክብሮም በርኸ በፖሊስ መወሰዳቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 10፣ 2013 ― የባይቶና ትግራይ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ክብሮም በርኸ ዛሬ ጧት አንድ ሰዓት ገደማ ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊስ መወሰዳቸውን አውሎ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

አምስት ፖሊሶች አቶ ክብሮምን መኖሪያ የጦር መሳሪያ ደብቀሃል በሚል ፍተሻ በማካሄድ ትፈለጋለህ በማለት ወደ ቱሉ ዲምቱ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዷቸውም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ፖሊሶች ፍተሻ ባካሄዱበት የፖለቲከኛው መኖሪያ ቤት ያገኙት ነገር የለም የተባለ ሲሆን፣ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ አቶ ክብሮም በቱሉ ዲምቱ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ ነው የተባለው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img