Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ መንግሥት ከትናንት እሁድ ምሸት ጀምሮ የማህበራዊ ሚዲያ ድረ-ገፆች ላይ እቀባ ጣለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 9፣ 2013 ― ከትናንት ምሽት ጀምሮ የፌስቡክ፣ ኢንስታግራምና ዋትስአፕ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች በኢትዮጵያ እቀባ እንደተጣለባቸው ማወቅ ተችሏል። የኢንተርኔት ስርጭትና አፈናዎችን የሚከታተለው ኔት ብሎክስ የተሰኘው ድርጅትም አገልግሎቶቹ መቋረጣቸውን አረጋግጧል።

ተጠቃሚዎች አገልግሎቶቹን የቪ.ፒ.ኤን ሽፋን የሚሰጡ መተግበሪያዎችን ብቻ በመጠቀም እንደሚያገኙ ተጠቁሟል። አገልግሎቶቹ ስለመቋረጣቸውም ሆነ ስለተቋረጡበት ምክንያት ከመንግስት በኩል እስከአሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።

መንግሥት ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች በተከሰቱ ቁጥር የኢነተርኔት አገልግሎትን እንደሚያቋርጥና የማህበራዊ ሚዲያ ድረ ገፆች ላይም በተደጋጋሚ እቀባ እንደሚጥል የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ሀገሪቱ ልታገኝ ተችል የነበረውን ከፍተኛ ገቢ ስታጣ ቆይታለች።

ኢትዮጵያ በ2020 ለ64 ቀናት ወይም ለ1 ሺሕ 536 ሰዓታት ኢንተርኔት በማቋረጧ የተነሳ 11̄1.3 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን አንድ ጥናት ያመለከተ ሲሆን፤ የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በተቀሰቀሰ ሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ ባለፈው ዓመት ሰኔ እና ሐምሌ ወራት ውስጥ ብቻ ከሦስት ሳምንት በላይ ኢንተርኔት ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img