Monday, November 25, 2024
spot_img

አሜሪካ በትግራይ ወታደራዊ ኃይሎች እርዳታ እንዳይሠራጭ ማድረጋቸው አሳስቦኛል አለች

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ግንቦት 8፣ 2013 ― አሜሪካ በትግራይ ወታደራዊ ኃይሎች እርዳታ እንዳይሠራጭ ማድረጋቸው እንዳሳሰባት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊው አንቶንዮ ብሊንክን ተቀባይነት የለውም ያሉት ይህ ተግባር በክልሉ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎችን ይበልጥ ችግር ውስጥ የሚከት መሆኑን አመልክተዋል።

ብሊንክንበ መግለጫቸው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ይኸው ሁኔታ እንዲስተካከል አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።
አክለውም ሁለም አካላት የተኩስ አቁም አድርገው በክልሉ የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እንዲደርስ ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img