Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ለኩላሊት ሕክምና የሚረዳው መድሃኒት ዋጋ ከሦስት ዕጥፍ በላይ ጨመረ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 7፣ 2013 ― የኩላሊት እጥበት ሕክምና እጥበት ለሚያደርጉ የሚሠጠው ‹‹ሄፓሪን›› የተባለው መድሃኒት ከዚህ ቀደም በመደብሮች ይሸጥበት ነበር ከተባለው 200 ብር ገደማ አሁን ከአንድ ሺሕ ብር በላይ እየተሸጠ እንደሚገኝ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ከኩላሊት ሕሙማን በጎ አድራጎት ድርጅት ሰምቻለሁ ብሏል፡፡

እንደ ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ከሆነ፣ የመድሃኒቱ ዋጋ ከሦስት እጥፍ በላይ የጨመረው ለኮቪድ ታማሚዎች ጭምር የሚሰጥ በመሆኑ ነው፡፡ በአገሪቱ በአሁኑ ወቅት በኪቪድ ተጠቅተው በጽኑ ታማሚዎች ክፍል የሚገኙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ ሰበብ የመድሃኒቱ ተፈላጊነትም በዚያው መጠን መጨመሩን አቶ ሰለሞን አስረድተዋል፡፡

ይህንe ተከትሎም የኩላሊት እጥበት ሕክምና የሚያደርጉ ሰዎች አገልግሎቱ ቀድሞም ከሚያስከፍለው ከፍተኛ ዋጋ ጋር ተዳምሮ የመድሃኒቱ ዋጋ ሲጨምር ከፍተኛ ጫና በመፍጠሩ፣ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ መሆኑንም አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img