Monday, October 7, 2024
spot_img

የተባበሩት መንግሥታት ከኢሰመኮ ጋር በጥምረት በትግራይ የሚያደርገው ምርመራ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይጀመራል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 7፣ 2013 ― የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጥምረት በትግራይ ክልል የሚያደርገው ምርመራ ሊጀመር መሆኑ ተነግሯል፡፡

በእንግሊዝ አፍ የሚታተመው ሪፖርተር እንደዘገበው በሁለቱ አካላት በክልሉ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራው በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይጀመራል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እንደገለጹትም የተባበሩት መንግሥተት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና ኢሰመኮ በክልሉ በጋራ ምርመራውን ለማድረግ ከተስማሙበት ጊዜ አንስቶ የዝግጅት ሥራዎች ሲከወኑ ቆይተዋል፡፡

በምርመራው ሂደት 12 መርማሪዎች ይሳተፋሉ የተባለ ሲሆን፣ ከሁለቱም ወገን ስድስት ሰዎችን የሚያካትት ነው፡፡ እነዚህን 12 መርማሪ ቡድን አባላት የሚያግዙ ተጨማሪ የተለያዩ ባለሞያዎችም እንደሚሳተፉበት የተነገረለት ምርመራ እስከ ሱዳን ሊዘልቅ ይችላል ተብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img