አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 7፣ 2013 ― በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ላይ በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ ተገንብቷል የተባለው የከተማ አውቶቡስ ተርሚናል በዛሬው እለት ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡
በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተርሚናል በአንዴ ለ20 አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት ያስችላል የተባ ሲሆን፣ ብዛታቸው 35 የሚደርሱ የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅት መስመሮች እና 17 ደግሞ ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት መስመሮች በድምሩ 52 መስመሮች ላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው፡፡
ይኸው የከተማ አውቶቡስ ተርሚናል በመርካቶ አካባቢ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመቀነስ በአንድ ሰዓት 6 ሺሕ፣ በቀን ደግሞ እስከ 80 ሺሕ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን አገልግሎት የሚያስችል መሆኑንም የከተማው ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡