Sunday, October 6, 2024
spot_img

በአማሮ ልዩ ወረዳ ከስድስት ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 7፣ 2013 ― በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች የታጠቁ ኃይሎች ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ከስድስት ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸው ተነግሯል፡፡

እንደ ዶይቸ ቨለ ዘገባ ከሆነ ነዋሪዎቹ ከትላንት በስትያ ጀምሮ አካባቢያቸውን እየለቀቁ የሚገኙት ረቡዕ ለሊት በሦስት ቀበሌዎች ማለትም በደርባ፣ ጉመሬ እና ቢፍቴ ወደ መንደር ዘልቀው የገቡ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገድለው ሌሎች ሁለት ማቁሰላቸውንና የመኖሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን ተከትሎ ነው።

ታጣቂዎቹ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጽሙ ይችላሉ በሚል ስጋት ነዋሪዎች አካባቢውን እየለቀቁ እንደሚገኙ የአማሮ ልዩ ወረዳ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ተወካይ አቶ አማረ አክሊሉ አረጋግጠዋል፡፡

ታጣቂዎች በየጊዜው በልዩ ወረዳው ነዋሪዎች ላይ የሚደርሱት ጥቃት እየተባባሰ ይገኛል የሚሉት የወረዳው ባለሥልጣናት በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ለችግሩ መፍትሄ ሊሰጥ አልቻለም ሲሉ ወቅሰዋል።

በደቡበ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተደጋጋሚ በንጹሐን ላይ ጥቃት እንደሚደርስ ዘገባው አስታውሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img