Friday, November 22, 2024
spot_img

የመቐለ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ የሰጡትን መግለጫ እንደሚደግፍ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 5፣ 2013 ― በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የመቐለ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ ትግራይ ክልልን አስመልክቶ ያወጡትን መግለጫ እንደሚደግፍ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ሀገረ ስብከቱ ባወጣው መግለጫ ከቀናት በፊት የቤተክርስትያኒቷ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ ከብዙ አፈና በኋላ ሰጥተውታል ያለውን መግለጫ ከዚህ ቀደም እንዳይሰጡ መደረጉን በኢትዮጵያ አፈና መኖሩን ያረጋገጠ ነው ብሎታል፡፡

እድሜና ጾታን ሳይለይ ዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እየተፈጸመ ነው ያለውን ጥቃት ያወገዘው ሀገረ ስብከቱ፣ ጥቃቱን ምክንያታዊ የሌለው ነው ብሎ የገለጸው ሲሆን፣ በሴቶች ላይ ደርሷል ያለውን ጥቃት ደግሞ ‹‹አረመኔያዊና ታሪክ የማይረሳው›› መሆኑንም አመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል ሀገረ ስብከቱ በትግራይ ክልል ላይ ‹‹ጭፍጨፋና ወረራ›› በማካሄድ ‹‹ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ አማራ ሶማሌና ኤምሬትስ››ን ወንጅሏል፡፡

በዚሁ ጥቃት ወቅት የትግራይ ሕዝብ በደል ሲደርስበት አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ‹‹እንደከዳው›› የገለጸው ሀገረ ስብከቱ፣ ወቅቱ የበዓል ወቅት ቢሆንም ለትግራይ ሕዝብ ግን ጊዜው የሐዘን መሆኑን ገልጧል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መሪ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ማትያስ ከቀናት በፊት ትግራይን አስምክቶ የለቀቁት የ14 ደቂቃ ቪድዮ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img