Monday, November 25, 2024
spot_img

ዋትስአፕ ከነገ ጀምሮ አዲስ የአጠቃቀም መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 5፣ 2013 ― ዋትስአፕ ከነገ ጀምሮ በአጠቃቀም ውሎችና ሁኔታዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎም ተጠቃሚዎች ከነገ በፊት ዋትስአፕ ያስተዋወቃቸውን አዳዲስ ደንቦች መቀብል ይኖርባቸዋል ተብሏል።

አዲሱን መመሪያውን ወዳልተቀበሉ ተጠቃሚዎቸቹ ‘ተከታታይ’ የማስታወሻ መልዕክቶችን እየላከ የሚገኘው ዋትስአፕ፣ የሚያደረገው ለውጥ በቀዳሚነት ‘ቢዝነሶች’ ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ላይ የሚያተኩር ይሆናል ነው የተባለው፡፡

አዲሱን የዋትስአፕ ደንብ የማይቀበሉ ደንበኞች አካውንታቸው ባይዘጋም እንደ ቀድሞ የጹሑፍ መልዕክት መለዋወጥ አሊያም በድምጽ ወይም በቪዲዮ መደዋወል አይችሉም መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ማሻሻያው የመልዕክት መተግበሪያው ዋትስአፕ ከእህት ኩባንያው ፌስቡክ ጋር መረጃን መጋራት እንደሚጨምር ባለፈው ጥር ላይ ተገለጾ ቅሬታን ፈጠሮ የነበረ ቢሆንም፣ አዲሱ ውል ላይ ይህ ማሻሻያ እንደማይካተትበት ታውቋል።

አስተማማኝ ደኅንነት እንዳለው የሚነገርለት ዋትስአፕ፣ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የግንኙነት መስመር ሚስጥራዊነቱን የሚጠብቅ ሥርዓት ያለው ነው፡፡

ዋትሳፕ ቀደም ብሎ ባሠራጨው መልዕክት ስልክ ቁጥርና ሌሎች ዋትስአፕ ለመክፈት የሚያግዙ እንደ ሥም ያሉ መረጃዎች፣ የተጠቃሚዎችን የእጅ ስልክ ዓይነት፣ ተጠቃሚው የሚገኝበትን ቦታ የሚጠቁመውን የእጅ ስልኩን መገኛ ቁጥር (IP address) እና በዋትስአፕ በኩል የሚፈጸም ክፍያና የገንዘብ ዝውውር ለፌስቡክ ኩባንያ መጋራታቸውን አስታውቆ ነበር፡፡

ሆኖም ይህ የዋትስአፕ አዲስ የአጠቃቀም ደንብ እና መመሪያ የግል መረጃ አጠባበቅ ሕግ ባሉባቸው አውሮፓ እና ዩናይትድ ኪንግደም ተግባራዊ አይሆንም መባሉንም ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img