Monday, October 7, 2024
spot_img

የመራጮች ምዝገባ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 5፣ 2013 ― በመላው አገሪቱ በ11 ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

ቦርዱ የመራጮች ምዝገባው ይጠናቀቅባቸዋል ባላቸው በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በአፋር፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በሐረሪ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች፣ በሲዳማ እንዲሁም ሶማሌ ክልሎች ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች እንዲወስዱ በማለት ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ቦርዱ በተጨማሪም ‹‹ለዜጎች መረጃ የምታቀርቡ ሚዲያዎች፣ ማኅበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች እና የፓለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች የምዝገባ የመጨረሻው ቀን ዛሬ መሆኑን በማስታወስ ዜጎች ካርዳቸውን እንዲወስዱ እንድታበረታቱ›› ሲል ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img