Sunday, November 24, 2024
spot_img

ሁለት ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች የቅድመ ምርጫ ሪፖርት አወጡ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 5፣ 2013 ― በተያዘው ግንቦት ወር መጨረሻ ይካሄዳል ተብሎ እቅድ የተያዘለትን ምርጫ ከሚታዘቡ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች መካከል የሆኑት የሪፐብሊካን ኢንስቲትዩት እና ናሽናል ዲሞክራቲክ ኢንስቲትዩት የቅድመ ምርጫ ሪፖርት ይፋ አድርገዋል፡፡

ታዛቢዎቹ በምርጫው ሒደት ታይተዋል ያሏቸውን እንቅፋቶች የዘረዘሩ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል የጸጥታ መደፍረስ እና ማንነት ተኮር ግጭቶች፣ የአንዳንድ ክልል ባለሥልጣናት ተባባሪ አለመሆን፣ ራሳቸውን ከምርጫው ያገለሉ ፓርቲዎች መኖራቸውን እንዲሁም የኮሮና ወረርሽኝን አንስተዋል፡፡

ይህ ሁኔታ እንዲስተካከል ሁለቱ ታዛቢዎች የተለያዩ ምክር ሐሳቦችን አቅርበዋል፡፡ ከምክረ ሐሳቦቹ መካከል፣ የፌደራል እና ክልል ጸጥታ ኃይሎች የመራጮችን እና የምርጫ ሠራተኞችን ደኅንነት ለማረጋገጥ በቅንጀት እንዲሠሩ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ራሳቸውን ከግጭት፣ የጥላቻ ንግግሮች እና ተመሳሳይ ተግባራት እንዲያርቁ፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ እየተዛመተ የሚገኘውን የኮቪድ ቫይረስ ለመከላከል ምርጫ ቦርድ ከጤና ባለሞያዎች ጋር በመሆን የመከላከያ መንገዶችን እንዲቀይሱ እንዲሁም ሁሉም አካላት የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እንዲሠሩ ጠይቀዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img