Monday, October 7, 2024
spot_img

የደምቢዶሎው ተጠርጣሪ ከሕግ ውጭ በአስደንጋጭ ሁኔታ መገደሉን ኢሰመኮ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 4፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን አማኑኤል ወንድሙ የተባለ የወንጀል ተጠርጣሪ በአስደንጋጭ ሁኔታ በፀጥታ ኃይሎች በአደባባይ መገደሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡

ኢሰመኮ ተጠርጣሪው ትናንት ማክሰኞ ጥር 3 ከሕግ አግባብ ውጭ በሆነ አስደንጋጭ ሁኔታ ህዝብ እያየ በአደባባይ መገደሉን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የወጣት አማኑኤል ወንድሙ ግድያ ጉዳይ ትናንት የማህበራዊ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነው ያመሸው፡፡

ወጣቱ ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደደረሰበት የሚያሳዩ የምስል እና የተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) ማስረጃዎችም ሲዘዋወሩ ነበር፡፡ በቪዲዮዎቹ ወጣቱ የፊጥኝ (ወደ ኋላ) ታስሮም ይስተዋላል፡፡

ከሕግ ውጭ የሚደረጉ የትኞቹንም ዓይነት ግድያዎች አወግዛለሁ ያለው ኢሰመኮም ሁሉም ሕግ የማስከበር ዘመቻዎች በህግ አግባብ እንዲፈጸሙ አሳስቧል፡፡

ግድያዎቹ በህግ የበላይነት ላይ እምነትን ከማሳጣትም በላይ የተገኙ ውጤቶችን እንደሚቀለብሱም ነው ኮሚሽቱ ያስታወቀው፡፡

በመሆኑም የአማኑኤል ወንድሙ ግድያ ጉዳይ በአስቸኳይ ተመርምሮ በአጥፊዎች ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img