Sunday, September 22, 2024
spot_img

የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ እና የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ስምምነት ተፈራረሙ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 4፣ 2013 ― የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) እና የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ለመጪው ምርጫ በጋራ ለመስራት በትላንትናው እለት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር ሙሳ አደም እና የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ዓብዱልቃድር አደም ናቸው።

ሁለቱ ፓርቲዎች አስቀድመው በደረሱበት መግባባት መሠረት ሀገር አቀፍ ፓርቲ የሆነው የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ድምጽ ላለመከፋፈል በአፋር ክልል ዕጩዎቹን አለማቅረቡን አስታውቀዋል።

ሀገር አቀፍ ፓርቲው በአፋር ክልል የሚገኙ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ የአፋር ሕዝብ ፓርቲን ዕጩዎች እንደሚመርጡ እንደሚያደርግ የገለጸ ሲሆን፣ ተጣማሪው የአፋር ሕዝብ ፓርቲም ከክልሉ ውጪ ባሉ አካባቢዎች ተመሳሳዩን እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር ሙሳ አደም “የተፈራርምነው ስምምነት በተለይ ከዚህ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ የአፋር ህዝብ እና የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በጋራ ሁለቱም ማሸነፍ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የተደረገ ስምምነት ነው” ብለዋል።

ሁለቱ ፓርቲዎች ላለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ ውይይቶች ሲያደርጉ መቆየታቸውን የተናገሩት ዶ/ር ዓብዱልቃድር፤ ስምምነቱን ለፓርቲያቸው ‹‹አንድ ትልቅ ዕድል›› መሆኑን ተናግረዋል። ስምምነቱንም ‹‹ታሪካዊ›› ሲሉ ጠርተውታል።

‹‹ነእፓ ትኩረት ከሚሰጣቸው የማህብረሰብ ክፍሎች አንዱ የሆነው የአርብቶ አደር ማህበረሰብን የልማት፣ የዲሞክራሲና የሰላም ጥያቄ ለመፍታት ከፓርቲው ጋር ብዙ አይነት ድርድሮች ስናደርግ ቆይተናል። በስምምነቱ ሰነድ ላይ እንደተገለጸው አንዱና ቁልፍ የነበረው የምርጫ ጉዳይ ነበር። ይሄ ስምምነት መፈረም የነበረበት የዕጩዎች ምዝገባ ከመደረጉ በፊት ነበር። በተለያዩ ቴክኒካል እና ሌሎች ምክንያቶች ወደ ዛሬ ዘግይቷል›› ማለታቸውን የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img